all silde

ተጀመረ


የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋትና ለሁሉም ለማድረስ በአሁን ጊዜ በአራት
የተከታታይ ሳይቶች የተከታታይ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የተከታታይ ትምህርትን
በዋና ግቢ፣ በዱራሜ እና በግልገል ጊቤ ቁ.2 ( Electrical Engineering ) መምህራንን በማሰማራት ተማሪዎች
በአቅራቢያ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አድርጓል፡፡ በያዝነውም በጀት ዓመት በ11 ትምህርት ክፍሎች፡-

 Management (BA)
 Accounting (BA)
 Economics (BA)
 English (BA)
 Civics and Ethical Education (BA)
 Hadyyisa (BA)
 Geography (BA)
 IT (BSc)
 Plant Science(BSc)
 Biology (BSc)
 Sport Science (BSc)

በሾኔ ከተማን ማዕከል በማድረግ በዙሪያ ላሉት ማህበረሰብ የተከታታይ ትምህርትን በቅርበት ለመስጠት ምዝገባውን
አጠናቅቆ ትምህርት መጀመሩን ስናበስርላችሁ ታላቅ ደስታ ይሰማናል፡፡
ከሁሉ በላይ ተማሪዎች ብዙርቀት በመሄድ የት/ት ደረጃቸውን ለማሻሻል ሲከፍሉ የነበረውን ከባድ መስዋዕትነት
በመቀነስ አሁን ባቅራቢያቸው ሥራቸውን እየሠሩ እንዲማሩ ዕድል በመስጠታቸው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲን ሳያመሰግኑ
አላለፉም ፡፡

መምህራኖችን በሳምንት መጨረሻ የእረፍት ጊዜያቸውን በመሰዋት በሀገራችን የሰለጠነ እና በስነ-ምግባሩ የታነፀ ዜጋ
ለማፍራት እየተደረገ ያለውን ርብርብ ለማፋጠን እና ውጤታማ ለማድረግ ቁርጠኞች መሆናቸውን
ገልጸዋል፡፡እንዲሁም በቀጣይ በግልገል ግቤ ቁ.3 የተከታታይ ትምህርት ለፕሮጀክቱ ሠራተኞች እና ለአካባቢው
ማሕበረሰብ በፍጥነት እና በጥራት ለማድረስ ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡

wachemo university
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Successful Discussion held with the “Place well HRD” Consultants

Dr. Habtamu Abebe, who is a vice president for Administration and Development and currently the A/ president of Wachemo University, held a fruitful discussion on international relation issues of the University with the international “Place well HRD Consultants (India)”. The delegates from the organization presented their mission that their organization is committed to attain. Their presentation focuses on ICT development, dairy farm, skill training for Hospital staffs and dual degree program for Wachemo University staffs who are in need of doing MA/ PhD.

The A/ president , along with the concerned staff members, had a fruitful discussion which may play a vital role in international relations of the university. It is believed that international relation is indispensable for an institution like Wachemo University. In the discussion, both parties agreed to conduct further discussion for the benefit and betterment of the institution.  

dr1 dr2

የዕውቀት ፋና

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ (ዋቼ) ከደቡብ ቴ/ሬ/ድርጅት የአየር ሰዓት በመግዛት ዘወትር ማክሰኞ ከ11--፡40-12፡00 የሚተላለፈውን “የዕውቀት ፋና” የተሰኘውን የሬዲዮ ፕሮግራም በ95.3 እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዝዎታለን ፡፡ይህ ፕሮግራም እጅግ አዝናኝና አስተማሪ ከመሆኑም በላይ ወቅታዊ መረጃን ለአድማጮች በማድረስ ረገድ ትልቅ ሚና አየተጫወተ ይገኛል፡፡ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች የሚያተኩሩት በዩኒቨርሲቲው መማር ማስተማር የጤና ነክ ትምህርቶች፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች፣የቴክኖሎጂና የምርምር ውጤቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር ልዩልዩ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በተለያዩ ክበባት ይቀርባሉ፡፡ ለአብነትም ያክል የተለያዩ ይዘት ያላቸው ግጥሞች፣ጭውውቶች፣ የመጣጥፍና መነባነብ ጽሑፎች አስተማሪና አዝናኝ በሆነ መልኩ ለአድማጭ ጆሮ ይቀርባሉ፡፡ብዙ አድማጭ እንደመኖሩ መጠን ከተለያዩ አድማጮች የምንቀበለው አስተያየቶች ለፕሮግራሙ ጥራት እንደ ግብዓት እንጠቀማለን፡፡

ይህንን የዩኒቨርሲቲያችን የብርሃን ጮራ የሆነውን የሬዲዮ ፕሮግራም እንድትከታተሉ ለሁላችሁም ጀባ ብለናል፡፡

south radio and televisison station

የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሄደ!

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ህብረት እና በሠላም   ፎረም መካከል የእግር ኳስ የወዳጅነት ጨዋታ ተካሄደ፡፡

የጨዋታውም ዓላማ ተማሪዎች እርስ በእርስ በሚያደርጉት ውድድር ከማዝናናትም ባሻገር በተማሪዎች መካከል የተጠናከረ ግንኙነትና ህብረት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነትና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ገለጹ፡፡

እስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሠ መልኩ ‘‘ሠላም ለሁላችን” በሚል መሪ   ቃል የተካሄደው ይህ ጨዋታ በዓይነቱ ልዩ መሆኑን በቦታው የተገኙ ታዳሚዎች በሰጡት አስተያየት ጨዋታው በአመት አንዴ ብቻ የሚደረግ ሳይሆን በዩኒቨርሲቲው የስፖርት ዲፓርትመንት አማካኝነት 6ቱም ኮሌጆች፣አዲስና ነባር ተማሪዎች ወዘተ… መካከል ቢደረግ መልካም ነው ብለዋል ፡፡

በጨዋታውም ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕ/ት ዶ/ር ሃብታሙ አበበ ከሠላም ፎረም በኩል የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ተ/ም/ፕ ዶ/ር ፀደቀ ላምቦሬ ከተማሪዎች ህብረት በኩል መጫወታቸው ለጨዋታው ልዩ ድምቀት ሆኖ ታይቷል፡፡

በመጨረሻም ጨዋታው 2-1 በሆነ ውጤትና ፍጹም ሰላማዊና ወንድማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቋል፡፡

Current ICT Project Progress

- Data center facilities

- High level devices implementation using hierarchical design (core to access level implementations)

- Storage configurations - Fiber and copper cabling facilies

- Video conference implementations

- VOIP configuarations

- Wireless campus implementations

- CCTV Cameras implementations.

Wachemo University Ict progress Wachemo University Ict progress Wachemo University Ict progress Wachemo University Ict progress